ፍሬህይወት አሰፋ- የ‹‹ፍሬ ጋርመንት›› መስራችና ባለቤት
—————
ፍሬህይወት በህክምና ትምህርት የተመረቀች ነርስ የነበረች ብትሆንም በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥራ በመስራት በምታገኘው ደሞዝ የኑሮ ሸክም ክብዷቸው የያሳደጓተን ቤተሰቦቿን ለማገዝ እንደማይበቃት አሳምራ ታውቃለች፡፡ ስለዚህ ከዚህ የተሻለ ገቢ የሚያስገኝ መፍትሄ መፈለጉ ተገቢ ነው ብላ አሰበች፡፡ ፊት ለፊቷ ያለው ብቸኛ አማራጭ ደግሞ ቤተሰቦቿ ያላቸውን ጥሪት ሰብስበው እርሷን በህገ ወጥ መንገድ ወደ አረብ ሃገር ለቤት ሰራተኝነት መላክ ነው፡፡
በህገወጥ መንገድ መግባቷን የሚያውቁት ባዕዳን ደግሞ የግፍ እንጀራ ብይ በለው ኑሮን አመረሩባት፡፡ ሲሻቸው ገንዘብ አይከፍሏቸውም፣ ሲያሻቸው ደግሞ አሳልፈው በህገወጥነታቸው ለመንግስት ፖሊሶች ይሰጧቸዋል፡፡ ፍሬም ከዚህ እጣ ፍንታ አለላመለጠችም አንድ አይሉ ሶስት ጊዜ አረብ ሃገራት በህገወጥ መንገድ ለመመለስ በቅታለች፡፡
የአረብ ሃገር የስደት ጎዞ ከዚህ በላይ የሚገፋ አይደለም፡፡ ራሷን ለሞት አሳልፋ እያወቀች መስጠት ደግሞ አልፈለገችም፡፡ ትርትር የምትል ጭላንጭል ተስፋዋ የዛሬዎን ፍሬን መሰረተቻት፡፡
በጣም በትንሽ ብር በአንዲት የስፌት መኪና ማሽን ወደ ፍሬ ጋርመንትን መሰረት ጣለች፡፡ መንግስት የፈጠረውን ምቹ ዕድል አይኗን ከፍታ ማየት ስትጀምር ይህ ሁለ ዕድል ነበረኝ እንዴ ስትል ራሷን እንደጠየቀችም ትናገራለች፡፡
ከእርሷ አልፎ ለሌሎች የእንደእሷ የአረብ ሃገር ኑሮ ገፍቶ የጣላቸው ሴቶችን መርዳት፣ ማሰልጠንና ምሳሌ በመሆን እንደእርሷ እንዲሆኑ ማቻሏ ደስታዋን እጥፍ ድርብ አደረገላት፡፡
ለስራዋ በምትሰጠው ትኩረት ምርቷን በርካታ ደንበኞች እንዲፈልጉት ምክንያት ሆኗል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ካፒታል የምታንቀሳቅሰው ፍሬ ከሃገራችን አልፎ በደቡብ ሱዳን፣ ደቡብ አሜሪካ ሃገራት ምርቶቿን በእጅ አዙር ቢሆንም ማደረስ ችላለች፡፡
‹‹ፍሬ ጋርመንት›› ዛሬ ላይ ከ40 በላይ ማሽኖች ያሉት እና ለበርካታ ሴቶችና ወንዶች የስራ ዕድል የፈጠረ ትርፈፋማና ምሳሌ የሚሆን ተቋም ነው፡፡
የስራ ፈጣሪዋ እንቅስቃሴ በቅርቡ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር በኢንጅነር አይሻ መሃመድና በፌደራል የከተሞች የሥራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በአቶ ገ/መስቀል ጫላ መጎብኘቱ ይታወሳል፡፡

By berhane

WEDP Communication specialist

Leave a Reply

Your email address will not be published.