የአንስተኛና መካከለኛ አምራችና አገልግሎት ሰጭ ተቋማትና አቅም ለማጎልበት የኢትዮጵያው የጂአይዜድ ቢሮ ድጋፍ ለማደረግ ከወዳደራቸው 124 ተቋማት ውስጥ የሴቶች ኢንትርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጀክት ሶስት ሴቶች አሸናፊ ሆኑ፡፡

በሃገር ደረጃ ካሸነፊት 18 ተቋማት ውስጥ ነው ሶስቱ የፕሮጀክቱ ደንበኞች አሸናፊ የሆኑት፡፡ ፕሮጅክቱ ከመስፈርቱ በመነሳት ከላካቸው 15 ደንበኞቹ መካከል የኤክስፐርትና የማሽነሪ ድጋፍ ያገኙት ደንበኞቹ ፕሮጀክታቸው የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ተጨባጭ በመሆንና ከስራው ጋር የሚሄድ ድጋፍ በመጠየቅ ተመርጠዋል፡፡ የፕሮፖዛል አቀራረቡም ግልፅ በሆነ ቋንቋ መቅረቡ ተመራጭ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

የመጀመሪያው የሆነው ይህ ፓይለት ፕሮጀክት በቀጣይም ለሌሎች እድል የሚሰጥ እንደሆነ ነው በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የተገለፀው፡፡

የፕሮጀክቱ አሸናፊ ጀከሆኑት መካከል ከአዲስ አበባ ማርሸት ፀሃይና ሩት ዮሐንስ ሲሆኑ ከአዳማ ደግሞ ማርታ ከበደ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ሶስቱ ሴቶች ሶሰት ሚሊዮን ስልሳ አንድ ሺ ብር በላይ ድጋፍ አግኝተዋል፡፡ ባገኙት ገንዘብም ድርጅታቸውን በማሻሻል አሁን ካሉበት ደረጃ በላቀ የሰው ሃይ በመቅጠርና ትርፋማ በመሆን ውጤታማ ይሆናል ተብሉ ይጠበቃል፡፡

By berhane

WEDP Communication specialist

Leave a Reply

Your email address will not be published.