በአዳማ ከተማና በዙሪያው በሚገኙ እንደ ዴራ ያሉ ቀበሌዎችን ጨምሮ ከ150 ሴቶች በላይ ሴቶች የኢንተርፕሪነርሽፕ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን ስልጠናውን ማግኘታቸው በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን ንግዳቸውን በተሸለ ሁኔታ እንዲቀጥሉ እንደሚያግዛቸው በስፍራው ተገኝተን ያነጋገርናቸው ሰልጣኝ ሴቶች ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በአዲስ አበባና በአሰላ ከተሞችም ስልጠናው ተጠናክሮ ሲቀጥል በተለይ በአዲስ አበባ በኮቪድ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የሞያ ስልጠና እንደገና ተጀምሯል፡፡ በምስራቅ ፖሊ ቴክሊክ ኮሌጅ ብቻ 60 የሚሆኑ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ በጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም በውበት ሳሎን ዘርፍ የሞያ ስልጠና እየወሰዱ ነው፡፡

በስፍራው ተገኝተን ካነጋገርናቸው ሰልጣኞች መካከል የጨርቃጨርቅና አልባሳት ሰልጣኝ የሆነችው የዛብነሽ ገበየሁ ባለፉት ወራት ያገኘችው ስልጠና በንግዱ አለም የተሻለች ተወዳዳሪ እንደሚያረጋት ገልፃልናለች፡፡

የቆዳ ቦርሳ እየሰራች ያገኘናት ሌላኛዋ ሰልጣኝ አበባ አዳነ ስልጠናው ክህሎቷን እደጨመረላት ትናገራለች፡፡

በቀጣይም በሁሉም የፕሮጀክቱ መገኛ ከተሞች ስልጠናዎች ተጠናክረው የሚሰጡ ሲሆን እድሉን ያላገኙ ሴት ኢንተርፕሪነሮች በስልጠናው ላይ በመሳተፍ ንግድና አገልግሎታቸውን የበለጠ ሊያጠናክሩበት ይገባል እንላለን፡፡

ለበለጠ መረጃ 8658 የነፃ የስልክ ቁጥር ይደውሉ

Ababa Adane – leather Training

By berhane

WEDP Communication specialist

Leave a Reply

Your email address will not be published.