በአዲስ አበባ በፌዴራል የተሞች የሥራ እድል ፈጠራ እና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ እና የፌደራል አንስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለስልጣን አዘጋጅነት በጀሞ አንድ አደባባይ አካባቢ እና በሜክሲኮ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት እየተካሄዱ የሚገኙት ኤግዚቢሽንና በዛር ላይ ከ25 በላይ ሴት ኢንተርኘሪነሮች ምርታቸውን አቅርበው እያስተዋወቁና እየሸጡ ነው፡፡በተመሳሳይ የአዳማ ከተማ ነጋዴ ሴቶች ማህበር አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ባለው ኤግዚቢሽንና በዛር ላይ ከ20 የሚደርሱ የአካባቢው ነጋዴዎች በኘሮጀክቱ ድጋፍ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ከመቶ ሺህ ብር በላይ በማውጣት ሴቶች ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደረገው ኘሮጀክቱ በቀጣይም በሌሎች ከተምች የሚገኙ ደንበኞችን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ እስከ ታህሳስ መጨረሻ 2013 ዓ.ም በመካሄድ ላይ በሚገኙት ኤግዚቢሽንና በዛሮች በመሳተፋቸው ሴቶቹ ደስታቸውን ገልፀውልናል፡፡ በዚህ ኤግዘቢሽንና ባዘር የገና በዓልን የሚያደምቁ በጥራት የተመረቱ የተለያዩ የቤት እቃዎች፣አልባሳት፣ የባልትና ዉጤቶች፣ቆዳና የቆዳ ዉጤቶች እና የአግሮ ፕሮሰሲነግ ምርቶች በስፋት ሴት ኢንተርኘሪነሮች ይዘው ቀርበዋል፡፡

By berhane

WEDP Communication specialist

Leave a Reply

Your email address will not be published.