የኢትዮጵያ መንግስትና የዓለም ባንክ በጋራ የሚያካሂዱት ፕሮጀክቱ ላለፉት ሰምንት ዓመታት ከ40 ሺ በላይ ሴት ኢንተርፕሪነሮችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ከ4.6 ቢሊዮን ብር ላይ ብደር ለሴቶች አቅርቧል፡፡

በዚህም በርካታ ሴቶች በጥቂት ካፒታል ተነስተው ዛሬ ላይ ሚኒየነር እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል፡፡

እስከ 2024 እ.ኤ.አ የሚያቆይ የ100 ሚሊዮን ዶላር ብደር የኢትዮጵያ መንግሰትና የዓለም ባንክ ተፈራርመዋል፡፡

ከተገኘው ብድር ውስጥ 70 በመቶ የሚሆነው ለሴቶች ብድ የሚውል ሲሆን ለሳይኮ ሜትሪክ ቴስት ለተባለው የፕሮጀክቱ ያለኮላተራል ብድር ማስኪያጂያና ለኮቪድ 19 – ኮረና ወረርሽኝ ማገገሚያ 10 በመቶ እያንዳንዳቸው በጀት ተይዞላቸዋል ብለዋል የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዮሃንስ ለሎሞን፡፡

ፕሮጀክቱ ለሚሰጠው ስልጠና ሶስት በመቶ በጀት የተያዘለት ሲሆን ሁለት በመቶ ከአጠቃላይ በጀቱ ለፕሮጀክቱ የሥራ ማስኪያጂያ ይውላል ተብሏል፡፡

በቀጥይ የፕሮጀክቱ  ቆይታም ከዚህ ቀደም ከነበሩ ከተሞች በተጨማሪ ሌሎች ሰምንት ከተሞች ተካተው ተጠቃሚ የሚሆኑ ሲሆን አምሰት ከተሞች ደግሞ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡    

By berhane

WEDP Communication specialist

Leave a Reply

Your email address will not be published.