መቐለ 19፣የካቲት 2009 ዓ.ም ፡ በመቐለ ከተማና አካባቢዋ በሴቶች ኢንተርፕሪነርሺፕ የሚፈጠረውን የስራ እድል ለማስፋፋት የባለድርሻ አካላትን የሳተፈ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክና የባለሞያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የፌደራል ከተሞች ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘነበ ኩሞ የሴቶች በመድረኩ ላይ እንደገለፁት ኘሮጀክቱ የራሳቸውን ስራ ፈጥረው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሴት ኢንትርፕረርነሮችን በፕሮጅክቱ ተጠቃሚ በማድርግ ስራቸውን ከማስፋት ባለፈ ተጨማሪ የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ ማገዝ ከአመራሩና ከፈፃሚው አካል ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የሴቶች ኢንተርፕሪነርሺፕ የልማት ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዮሐንስ ፕሮጅክቱ የፋይናስ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ሙያዊና የክህሎት ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ እንዲሰማሩ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በተለይ  በአቅም ግንባታ፣ በሙያዊና የክህሎት ስልጠናዎች፣ በሂሳብ፣ በንግድ ስራ ውጤታማነትና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ስልጠናዎችን እየሰጠ በሙሉ አቅሙ እየሰራ ከመሆኑም በላይ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ማሰራጨቱን ጠቁመዋል፡፡

የመቐለ ከተማ ጥቃቅንና አንሰተኛ ንግድ ተቋማት እና የከተማ ምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ልዕልቲ ፍስሃ በከተማ ደረጃ የተጠቃሚዎች ቁጥር በእጥፍ ለማሳደግ የባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ንቅናቄ መጀመሩን ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በአቅም ግንባታ ስልጠና እና በንግድ ስራ ስልጠና እንዲሁም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትና በብድር ማሰራጨትና ማስመለስ ዙሪያ ወሳኝ ሚና በመጫዎት ለፕሮጀክቱ ዓላማ ስኬት የድርሻቸውን ሊወጡ ስለሚገባ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ነው ያሉት።

ፕሮጀክቱ እስከ 2010 ዓ ም መጨረሻ ድረስ የሚቆይ  መሆኑን ያመለከቱት አስተባበሪው ቀጣይነቱ በሚኖረው ውጤትና በለጋሾች ድጋፍ ዘለቄታነት የሚወሰን በመሆኑ ለስኬታማነቱ የጋራ ጥረት እንደሚጠይቅ አስተባባሪው አቶ ዩሃንስ ገልፀዋል፡፡

በዚህም በዘርፉ የተሰማሩ ሴት ኢንተርፕርነሮች ከራሳቸው አልፎ በከተማዋ ለሚገኙ ዜጎች የስራ እድል መፍጠራቸውን ገልፀዋል።

የሴቶች ኢንተርፕሪነርሺፕ የልማት ፕሮጀክትሥራ የጀመረው ከኢትዮጵያ መንግስት የልማት ተቋማትና ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተገኘው 58 ሚሊዮን ዶላር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለአምስት ቀናት የቆየ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አንድ ማዕከል ባለሞያዎች የተሰጠ ሲሆን ሴት ኢንተርፕርነሮችን ወደ ስልጠና በስፋት እንዲገቡ የሚያግዝ የኮሙኒዮኬሽን ስልጠና ተስጥቷል፡፡

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published.