የሴቶች ኢንተርፕረነርሽኘ ልማት ፕሮጀክት የስራ እንቅስቃሴ የሚደግፈው የካናዳ መንግስት የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ ሴቶች ያሉበትን ደረጃ ለመመልከት የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደርን ጨምሮ በባህር ዳር ሚያዚያ 14፣ 2009 ዓ.ም ተገኝተዋል፡፡

በባህር ዳር ከተማ ያሉ ብድርና ስልጠና ያገኙትን ውጤታማ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ሴቶችን በስራ ቦታቸው ተገኝተው የጉበኙ ሲሆን በተመለከቱትም ደስተኞች እንደሆኑ ነው ሚኒስትር ዴኤታው የገለፁት፡፡

በማኑፍክቸሪንግ ዘርፍ፣ በንግድና በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ሶስት ሴት ኢንትርፕርነሮች የተጎበኙ ሲሆን ባገኙት ስልጠና እና ብድር በመጠቀም ከነበሩበት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ አሁን ላይ ወደ ተሻለ ህይወት እያመሩ እንዳለ ለተገኙት እንግዶች ገልፀውላቸዋል፡፡ በዋነኝነት የብድር አገልግሎት ለማግኘት የማስያዥያ (ኮላተራል) ችግር እያጋጠማቸው እንዳለ ነው ለእንግዶቹ ያብራሩት፡፡

ይህንን ችግር ለመፍታት ፕሮጅክቱ አዲስ አሰራር እያስተዋወቀ እንዳለ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ዩሃንስ ሰሎሞን ተናግረዋል፡፡ ከአበዳሪ ተቋማቱ ጋር አብሮ በመስራት በሳይኮሜትሪ ፈተና ሴቶችን በመመዘን ፈተና ያለፉ ሴት ኢንትርፕርነሮች ያለ ዋስትና ወይም በዝቅተኛ ዋስትና ብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ እየተመቻቸን ነው ብለዋል አቶ ዩሃንስ፡፡

የሴቶች ኢንትርፕረነርሽፕ ልማት ፕሮጀክት ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት እንዲራዘም የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ለዓለም ባንክ ጠየቀ፡፡

በኢትዮጵያ የተገኙት የዓለም ባንክ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ የሚገኙ የሴቶች ኢንትርፕረነርሽፕ ልማት ፕሮጀክት ተጠቃሚዎችን ጎብኝተዋል፡፡

አዲስ አበባ መጋቢት 25፤ 2009 ዓ.ም የዓለም ባንክ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በኢትዮጵያ ተገኝተው የሴቶች ኢንትርፕረነርሽፕ ልማት ፕሮጀክትን የገመገሙ ሲሆን እያከናወነ ባለው ተግባርም ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ከከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ጋር በነበራቸው ቆይታም ፕሮጀክቱ ለሌሎች ሃገራትም ጥሩ ምሳሌ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡ በተለይም የኢንዶኔዥያ መንግስት ተመሳሳይ ፕሮጀክት ለመተግበር ሃሳቡን መቀበሉ በውይይቱ ወቅት ሃላፊዎቹ ለሚኒስትሩ ገልፀውላቸዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ይህንን ፕሮጀክት ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ለማስቀጠል የዓለም ባንክን ጠይቋል፡፡ የዓለም ባንክም ጥያቄውን እንደሚቀበለው ይታመናል፡፡

በተጨማሪም የዓለም ባንክ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ የሚገኙ የሴቶች ኢንትርፕረነርሽፕ ልማት ፕሮጀክት ተጠቃሚዎችን ጎብኝተዋል፡፡ ስራቸው የተጎበኘው ሴት ኢንትርፕረርነሮችም ፕሮጀክቱ ምን ያህል እየጠቀማቸው እንዳለ ገልፀውላቸዋል፡፡

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published.