የሴቶች ኢንትርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጀክትና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ የልምድ ልውውጥ ላይ እስከ 12 የሚደርሱ የብድር ማስያዥያ (ኮላተራል) እንዳለው የዘረዘረው አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም ለሌሎች አርያ የሚሆን ተሞክሮ አቅርቧል፡፡

በውይይቱ ላይ የአለም አቀፍና የሃገራችን ልምድ ቀምሮ ያቀረበው ኢንትርፕሪነርሽፕ ፓርትንር ተቋም ይህንን መሰል የልምድ ልውውጥ መደረጉ ሴቶች በተለያ አማራጮች ብድር እንዲያገኙ ያግዛቸዋል ብሏል፡፡  

 በውይይቱ ላይ የተገኙት የፌደራል ከተሞች ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘነበ ኩሞ በብድር አሰጣጥና ተቋማቱ አሰራር ላይ ፕሮጀክቱ ጣልቃ ገብ ባይሆንም ለሴቶች ችግር መፍትሄ በመስጠቱ በኩል ግን አማራጭ ላይ መምከሩ አዋጭ መሆኑን ያምናል ብለዋል፡፡

ዛሬ ላይ ከወሳሳ ማይክሮፋይናስ የዓለም ባንክ እየሞከረው ያለው የሳይኮሜትሪክ ቴስት ( የተበዳሪዋን ፍላጎት መዝኖ ያለ ማስያዥያ ኮላተራል ማበደር) እስከ 15 ለሚሆኑ ሴቶች በመስጠት የጀመርነው ቢሆንም ይህ ሙከራ እንጂ በሁሉም አካባቢ እየተተገበረ ያለ አይደለም፡፡ ነው ያሉት፡፡

በውይይቱ  የብድር ማስያዥያ አሰራር ልምድ ባንኮቹ የተለዋወጡ ሲሆን ለሴቶች የተሻለ የሚሉትን አሰራር እንዲዘረጉ  ያግዛቸዋል ተብሏል፡፡

By admin

One thought on “የሴቶች ኢንትርፕሪነርሽፕ ልማት ፕሮጀክት ጋር በጋራ የሚሰሩ 12 የአንስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት የብድር ማስያዥያ (ኮላተራል) ልምድ ልውውጥ አካሄዱ፡፡”

Leave a Reply

Your email address will not be published.